free book gift

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።


Iqra

=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=

ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ


1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።

2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።

3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።

4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
Iqra
Iqra

Homeየወጣቱ ተልዕኮ ምንነትየአቂዳ ትምህርቶችየሶላት መመሪያረመዷንሙስሊም ሴቶችኢስላማዊ ቤተሰብከታሪክ ማህደርሐዲስለወጣቶችትምህርትና መሰረታዊ ክህሎታችጤናችንግጥምጥያቄና መልስኢስላማዊ መዝገበ ቃላት
free book gift

=<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=

ያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም አንብብ!

free book gift

በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።

free book gift

እውነተኛ ሃይማኖት


✍አዘጋጅ: አቡ አሚና ቢላል ፊሊፕስ
ተርጔሚ: ጀማል ሙኽታር

ክፍል 1 Iqra
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

የእስልምና ሃይማኖት

ኢስላምን አስመልክቶ አንድ ሰው በቅድሚያ ሊያውቀውና በግልፅ ሊረዳው የሚገባው ነገር ኢስላም የሚለው ቃል ትርጉሙ ራሱ ምን ማለት እንደሆነ ነው። ክርስትና ከእየሱስ፤ ቡድሂዝም ከጉተማ ቡድሃ፤ ኮንፊሽያኒዝም ከኮንፊሽየስ እንዲሁም ማርክሲዝም ከካርል ማርክስ ስያሜያቸውን እንዳገኙ አይነት የእስልምና ሃይማኖት ስሙን ከግለሰብ ስም አልወሰደም። እንደ አይሁዳ ከይሁዳ ጐሳና እንደ ሕንዱይዝም ከህንዱ መጠሪያ ስሙን አላገኘም። ኢስላም የአሏህ ሃይማኖት ነው። በመሆኑም መጠሪያ ስሙ የአሏህን ሃይማኖት ማእከላዊ መርህ ለአሏህ ፈቃድ ሙሉ በሙሉ መገዛትንና ማደርን የሚወክል መጠሪያ ስም ነው። ኢስላም የሚለው የአረብኛ ቃል አምልኮት ለሚገባው ብቸኛ እውነተኛ አምላክ ለአሏህ ራስን ማስገዛትና ለርሱ ፍቃድ ማደር ማለት ሲሆን ይህን የሚያደርግ ማንኛውም ሰው «ሙስሊም» ተብሎ ይጠራል። በተጨማሪም ቃሉ ሙሉ በሙሉ ለአሏህ ፈቃድ የመገዛት ውጤት የሆነውን "ሠላምን" ያመለክታል። ስለዚህ ዐረቢያ ውስጥ በሰባተኛው ክፍለ ዘመን በነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) አማካኝነት የመጣ አዲስ ሀይማኖት ሳይሆን በመጨረሻ ቅርፁ ዳግም የተገለፀ እውነተኛ ሀይማኖት ነው።

ኢስላም ለመጀመሪያው ሰውና ለመጀመሪያው የአላህ ነቢይ ለአደም የተሰጠና ወደ መላው የሰው ልጅ ከአሏህ የተላኩ ነቢዮች ሁሉ የጋራ ሃይማኖት ነዉ። የአሏህ ሃይማኖት የሆነው ኢስላም በዚህ እንዲሰየም የተወሰነው በኋለኞቹ የሰው ልጅ ትውልዶች አይደለም። ስሙ የተመረጠው በራሱ በአሏህ ሲሆን ይህም ወደ ሰው ልጅ ባስተላለፈው የማጠቃለያ መልእክት(ወሕይ) ውስጥ በግልፅ ተጠቅሷል። የመጨረሻው መለኮታዊ መፅሐፍ በሆነው ቁርአን ውስጥ አሏህ እንዲህ ይላል፦

=<({ሱራ አል-ማኢዳ 5:3})>=


{3} ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ ጸጋየንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ ለናንተም ኢስላምን ከሀይማኖት በኩል ወደድኩ።

=<({ሱራ አል-ዒምራን 3:65})>=


{65} ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈፀጽሞ ከርሱ ተቀባይነት የለውም፤

=<({ሱራ አል-ዒምራን 3:67})>=


{67} ኢብራሂም ይሁዳዊም ክርስቲያንም አልነበረም ግን ወደ ቀጥተኛው ሃይማኖት የተዘነበለ ሙስሊም ነበር፤

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የትም ቦታ ላይ አሏህ ለነብዩ ሙሳ ሕዝብም ሆነ ለዝርዮቻቸው የነርሱ ሃይማኖት ይሁዳዊነት ነው ሲል ወይም ለክርስቶስ ተከታዮች ሃይማኖታቸው ክርስትና ነው ሲል አናገኝም። እውነቱን ለመነጋገር ሌላው ቀርቶ "ክራይስት" የሚለው ቃል "ክርስቶስ" ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ስም ሲሆን ትርጉሙ የተቀባው ማለት ነው። ይህም ክርስቶስ "መሲሕ" ለሚለለው የዕብራይስጥ የማእረግ ስም ትርጉም ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ኢየሱስ የሚለው ስም "ኢሳው(Esau)" ለሚለው የኢብራይስጥ ስም ላቲናዊ ቅላፄ ነው።

ይሁን እንጅ ነገሩን ቀላል ለማድረግ ስል ነብዩ ኢሳ(ዐ.ሰ) እየሱስ ብየ መጥራቴን እቀጥላለሁ። ሃይማኖታቸውን በተመለከተ ግን መጠፈሪያው ነብዩ ተከታዮቻቸውን ይጠሩበት የነበረው ስም ነው። ከሳቸው በፊት እንደነበሩት ነቢያት ሁሉ ሕዝቡ ፍላጐቱን ለአሏህ ፍላጐትና ለርሱ ፈቃድ እንዲያስገዛ ጥሪ አድርገዋል። የሰው ልጅ ምናብ ከፈጠራቸው የሐሰት አማልክት እንዲርቅም አስጠንቅቀዋል።

በሐዲስ ኪዳን እንደተጠቀሰው ተከታዮቻቸው «ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነ እንዲሁ በምድርም ትሁን» ብለው እንዲፀልዩ አስተምረዋል።

የኢስላም መልእክት

Iqra

የራስን ፍላጐትና ፈቃድ ሙሉ በሙሉ ለአሏህ ማስገዛት የአምልኮትን ሥረ-መሠረት የሚወክል እንደመሆኑ መጠን የአሏህ መለኮታዊ ሃይማኖት የሆነው የኢስላም መሠረታዊ መልእክት አሏህን ብቻ ማምለክና ለማንኛውም ሰው ፣ ቦታ ወይም ከአሏህ በስተቀር ለማንኛውም ነገር ከሚደረግ አምልኮ ፈፅሞ መራቅ ነው። የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ ጌታ ከሆነው ከአሏህ በስተቀር ያለው ማንኛውም ነገር የአሏህ ፍጡር በመሆኑ የሰው ልጅ ከፍጡራን አምልኮ እንዲገታ ጥሪ በማድረግ የፍጡራን ፈጣሪን አምላክ ብቻ እንዲያመልክ መጋበዝ የኢስላም ተልእኮ ሥረ-መሠረት ነው ማለት ይቻላል። አምልኮውና ጸሎቱ ተቀባይነት የሚያገኙት በርሱ ፈቃድ ብቻ እንደመሆኑ የሰው ልጅ አምልኮ ሊቀርብለት የሚገባው ለአንድ አሏህ ብቻ ነው። ሰው ዛፍ ቢያመልክና ጸሎቱ ተሰሚነት ቢያገኝ ለጸሎቱ ምላሽ የሰጠው ዛፉ ሳይሆን የተለመነው ነገር እንዲፈጽም የፈቀደው አሏህ ነው። አንድ ሰው ለዛፍ አምላኪወች እንዲህ ሆኖ አይታያቸውም ሊል ይችላል በተመሳሳይ መልኩ ለእየሱስ ለቡድሃ ወይም ለክሪሽና ወይም ለሙሐመድም(ሰ.ዐ.ወ) ቢሆን የሚደረግ አምልኮና ጸሎት ምላሽ የሚሰጠው በነዚህ ሰወች ሳይሆን በአሏህ ነው። እየሱስ ተከታዮቻቸው በሳቸው እንዲያመልኩ አላስተማሩም፤ ያስተማሩዋቸው አንድ አሏህን ብቻ እንዲገዙ ነው። ቁርአን ይህንኑ ሲገልጽ እንዲህ ይላል፦

=<{(ሱራ አል-ማኢዳህ 5:116})>=


{116} አሏህም የመርየም ልጅ ኢሳ ሆይ! አንተ ለሰዎቹ እኔንና እናቴን ከአሏህ ሌላ ሁለት አምላኮች አድርጋችሁ ያዙ ብልሃልን በሚለው ጊዜ (አስታውስ) ጥራት ይገባህ ለኔ ተገቢዬ ያልኾነ ነገር ማለት ለኔ አይገባኝም።

ሲያመልኩ የነበረው የገዛ እራሳቸውን ሳይሆን አምልኮታቸውና ተገዥነታቸው ለአሏህ ብቻ ነበር። ይህ መሠረታዊ መርሕ ሱራ አል-ፋቲሀ 1:4 ውስጥ ተቀምጧል "አንተን ብቻ እንገዛለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታ እንለምናለን።" የመጨረሻው መለኮታዊ ራእይ(ወሕይ) መጽሐፍ በሆነው ቁርአን ውስጥ ሌላ ቦታ ላይ አሏህ እንዲህ ብሏል፦

=<({ሱራ አል-ሙእሚን 40:60})>=


{60} ጌታችሁም አለ: ለምኑኝ እቀበላችኋለሁና፤

አሏህና የርሱ ፍጥረታት ፍጹም የተለያዩ ሕላዌዎች ናቸው የሚለው የኢስላም መልእክት መሆኑን መገንዘብ በጣም አስፈላጊ ነው። አሏህ ፍጡር ወይም የፍጥረቱ አካል አይደለም። የርሱ ፍጡርም እርሱ ወይም የርሱ አካል አይደለም። ይህ አባባል ግልጽ ሊመስለን ይችላል፤ ነገርግን የሰው ልጅ ፈጣሪውን ትቶ ፍጡርን የሚያመልከው በአብዘኛው ይህን ጽንስ ሀሳብ ካለመረዳት የተነሳ ነው። አሏህ በሁሉም ቦታ ፍጥረት ውስጥ ሰርጿል ወይም መለኮታዊ ሕልውናው በአንዳንድ የፍጥረት ገጽታዎች ውስጥ ይገኛል የሚለው እምነት ነው። በዚህ አይነቱ አምልኮ አማካኝነት ፍጡሩን የማምለክና በፍጡር አማካኝነት የመጣው የኢስላም መልእክት አንድ አሏህን ብቻ ማምለክና በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ፍጡርን ማምለክ ማስወገድ ነው። አሏህ ቁርአን ውስጥ ይህንን ሲናገር እንዲህ ብሏል፦

=<({ሱራ አል ነሕል 16:36})>=


{36} በእርግጥ በሁሉም ሕዝቦች ዉስጥ አሏህን ተገዙ ጣዖትንም ራቁ በማለት መልእክተኛን ልከናል፤

በጣዖት የሚያመልከው ሰው በሰው እጅ ተጠርቦ ለተሠራ ጣዖት ለምን እንደሚሰግድ ሲጠየቅ ከቦታ ቦታ የማይለያይ ተመሳሳይ ምላሹ በተጨባጭ የምናመልከው ጥርቡን የድንጋይ ወይም የእንጨት ምስል ሳይሆን በርሱ ውስጥ የሰረፀውን አሏህን ነው የሚል ነው። ጥርቡ ድንጋይ ወይም እንጨት ጣዖት አሏህ ለሚለው ጽንስ ሀሳብ የትኩረታችን ማሳረፊያ ነጥብ እንጂ አሏህ ራሱ አይደለም ይላሉ። አሏህ በፍጡራን ውስጥ በሆነ መንገድ ሰርጿል የሚለውን ፅንስ ሐሳብ የተቀበለ ሰው ይህን የአምልኮተ ጣዖት ክርክር ለመቀበል ይገደዳል። የኢስላም መሠረታዊ መልእክትና አንድምታዎቹን የሚረዳ ሰው ግን የፈለገውን ያህል ምክኒያታዊ መስሎ ቢቀርብ በጣዖታዊነት ፈጽሞ አይረታም። በሁሉም ዘመናት ራሳቸውን የመለኮታዊነት ባህሪያት በራሳቸው ያላበሱ ወገኖች አሏህ በሰብአዊ ፍጡር ሰርጿል በሚል የተሳሳተ እምነት ላይ ነው አባባላቸውን የሚገነቡት። በተሳሳተ እምነታቸው መሠረት አሏህ በሁላችነም ውስጥ የሰረፀ ቢሆንም ቅሉ ከተቀሩት ሰዎች ይበልጥ እነርሱ ውስጥ የሰረጸ አድርገው ይናገራሉ። ስለሆነም ፍላጐታችነን ለርሱ ማስገዛት በአካል ወይም አምላክ ከመሆናቸው አንፃር ወይም አምላክ በነርሱ ስብእና ውስጥ የታመቀ ከመሆኑ አኳያ እነርሱኑ ማምለክ እንዳለብን ይለፍፋሉ።

በተመሳሳይ መልኩ እነዚያ የሰወችን አምላክነት ከሰዎቹ ሞት ቡሃላ የተቀበሉ ወገኖችም አምላክ በሰው ውስጥ ሰርጿል የሚለውን የተሳሳተ እምነት በሚቀበሉ ሰወች ዘንድ የሞቀ አቀባበል አግኝተዋል። የኢስላምን መሠረታዊ መልእክትና አንድምታዎቹን የተገነዘበ ሰው ግን በማንኛውም ሁኔታ ሰብአዊ ፍጡርን ማምለክ በጭራሽ አይቀበልም። የአሏህ ሃይማኖት በመሠረቱ ለፈጣሪ አምልኮ የሚደረግ ግልጽ ጥሪና የፍጡራንን አምልኮ በማንኛውም መልኩ ውድቅ ማድረግ ነው። ይህም የኢስላም መፈክር የሆነው "ከአሏህ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም" የሚለው ነው።

ይህን መናገር አንድን ሰው በቀጥታ ወደ ኢስላም ጐራ ሲያመጣ፤ በፍጹምነት በዚህ አምኖ ከልቡ መቀበል ጀነት የመግባት ዋስትናን ያስገኝለታል። መፈክሩ አሏህን አንድ ብቸኛ አምላክ አድርጐ ለርሱ ብቻ መገዛትን ፣ ለሕግጋቱ መታዘዝን ፣ ጣዖታዊነትንና ጣዖታዊያንን ማስተባበልን ያካትታል።

Iqra
Iqra Iqra Iqra Iqra Iqra Iqra
Iqra
2883

የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
free book gift

Download Islamic Books
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ

Important Web Links


free book gift

free book gift

free book gift

ስለወጣቱ ተልዕኮ ምንነት ለማወቅ እዚህ ላይ ክሊክ ያድርጉ

Copyright©Youth-Mission የወጣቱ ተልዕኮ


Duck hunt